Showing 85–95 of 95 results

  • ከዕለታት ….ግማሽ ቀን

    $15

    አሌክስ አብርሃም በከዚህ ቀደም መጽሃፎቹ አሳምሬ አውቀዋላሁ። እንሆ ደግሞ አሁን ማለፊያ የብዕሩ የሕይወትን ማጀትና አደባባይ እንዳሻው ዕያሰሰ የሚያሳይበትን ትነቦ የማይጠገብ ዓይነተኛ የጽሁፍ በረከቶቹን ጀባ ብሎናል።

    Add to cart
  • ዙቤይዳ

    $14

    “አገር ማለት ሰው ነው እያሉ በትውልድህ እንቅልፍ ላይ ብርድ ልብስ ይደርባሉ። አገር ማለት አፈር ነው። ሰውም ማለት አፈር ማለት ነው። ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ የሞቱት ሰዎቻችን ስጋና አጥንት አፈር ሆኖ ይሄው” አሉና መሬቱን ብጎራዴው ጫፍ ጫር አደረጉት።

    Add to cart
  • የሃበሻ ጀብዱ

    $25

    ሃበሽስካ ኦዴሳ (Habešská Odyssea) – የሃበሻ ጀብዱ  መጽሐፍ የዚያን የገበሬ ጦር ጀግንነት ለመዘከር የጻፉት ነው።

    Add to cart
  • የመደመር መንገድ

    $20

    ሀገር የሚመራበት ሥርዓት ሚዛኑን ጠብቆ እንዲጓዝ የሚያስችሉት ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፤ ዋነኞቹ ግን ተቋማት ናቸው። እነዚህ ተቋማት ዐቅማቸው እየደከመ ሲሄድ በሥርዓቱ ውስጥ ግለሰቦች ጉልበታቸው እንዲፈረጥም ዕድል መፍጠሩ አይቀርም። ለምሳሌ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ዲሞክራሲ ሊወለድባቸው ገና ብዙ ትግል በሚቀራቸው ሀገራት ነጻ የፖሊቲካ እንቅስቃሴ ለማካሄድ ሜዳውን ለሁሉም ክፍት ማድረግ ብቻ አይበቃም። ሂደቱ ያለ ችግር እንዲከናወን፣ ግለሰቦች ያለመሸማቀቅና ያለጥቃት እንዲሳተፉ፣ የዲሞክራሲና የፍትሕ አካላት ሚዛን የመጠበቅ ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ የሥርዓቱ ሚዛን የሚጠበቀው በግለሰቦች በጎ ፈቃድ መልካም ስብእና ላይ ተመስርቶ ይሆናል።

    Add to cart
  • የስንብት ቀለማት

    $20

    የስንብት ቀለማት ስፍራን በምሳሌ ነድፎ ፤ በምስሎች ደንግጎ ፣ በፈገሮች ቆርጾ፣ በሐቲት ደረጃ እየተራቀቀ ጭምር ተመለከትነው። እንዲህ ባለ ምልዓትና ንቃት ሥፍራን መንደፍ… ለአገራችን ሥነ ጽሑፍ እጅግ እንግዳ ይመስለኛል።

    Add to cart
  • የታፋኙ ማስታወሻ

    $18

    ከጥቂት ሰአታት በረራ በኋላ ከዱባይ የተነሳው አውሮኘላን ሰነአ አሰም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረሰ። ሁሉም ተሳፋሪ ወረደ፡፡ ጥቂቱ ተሳፋሪ አዛው ሰነአ ቀሪ ነው፡:……. አኔም አንደሌሎች ተሳፋሪዎች በዚህ አውቶቡስ ላይ ተጫንኩ-: አውቶቡሱ ብዙ ርቀት አልፄደም። ከአንድ ህንጻ ፊት ቆመ: ተሳፋሪዎችን ተከትዬ እኔም ከአውቶቡሱ ወረድኩ: አነሉን ተከትዬ ወደ ህንጻው ተጓዝኩ: ለመጀመሪያ ጊዜ ክዚህ ጉዞ ጋር የተያያዘው ስጋቴ እውን ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ አየሁ።

    Add to cart
  • የአንድ ኃይል

    $18

    አንድ ትራፊክ ፖሊስ ሙሉ ትጥቁን አድርጎ መኪና በፍጥነት በሚርመስበት መገገድ መካከል ቆሞ የእጅ ምልክት ቢያሳይ የቱንም ያህል ልምድ ያለው ሹፌር፣ምንም አይነት የዋጋ ደረጃ ያለው መኪና፣ ለማጅ ሆነ ርካሽ መኪናን እኩል ያስቆማል፡፡ አንዲህ በዘመን ሆኖ የማያውቅ ነገር በ2012 አስተናግደናል፡፡ አንዲት ቫይረስ አለሙን በሙሉ ቀጥ አድርጋለች፡፡ ምናልባት 2ዐ12 ስሌትን የተማርንበት አመት ይመስለኛል፡፡ በአንድ አለሙ ሁሉ ቆሟል፡፡

    አንድ ስንት ሆነ? አንድን ነገር ከስሙ በላይ መጠየቅ በዓላማው መጠን መጠቀም መልካም ነው፡፡ ይህች መፅሐፍ ደንብራ ለነቃቶች ተለውጣ ለጠበቀችው አለም የአንድ ኃይልን በመጠቀም የሰው ለሰው ግንኙነት ወደአቅም የሚለውጥበትን ጥበብ ታካፍላለች፡፡ የአንድ ኃይል ምንድነው? ቤቴ፣ ትዳሬ፣ ግንኙነቴ፣ ዝምድናዬ ሁሉ የአንድ ኃይልን ተጠቅሞ አቅም መሆን ይችላል? በውስጥ ገፅ መልስ እናገኛለን፡፡ ምን ይታወቃል አንድ ኮቪድ 19 ስም አውጥተን በአለም ሁሉ አንዴ ፀጥ በሉና ስሙኝ በማለት ሊያስቆም ከታመነ፡፥ አንድ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ ተቋምም ሆነ ማህበር አንድ በመሆን ያለውን ሊሰማ በሚችል መጠን ለውጦ ለማቅረብ ቢተጋ እንዴት አለሙን በመድረስ መሰማት ያቅተዋል?

    አንድነት ከአንድ ይወለዳል!

    Add to cart
  • የከተማው መናኝ ኤልያስ መልካ

    $19

    “ተገርሜ አግብቶ ነበር እንዴ? ብዬ ጠየኩት። ቀለበት አስሮ ነበር ብሎ መለሰልኝ። ቀለበት ቀለበት? ስለው ሳቀ። ጣቱን እያመለከተ እኔ እንዳደረኩ ዓይነት ቀለበት አድርጎ ነበር መሰለኝ አለኝ። ማን ጋር ይሆን? ብዬ ለአፍታም አልተጠራጠርኩም። የፍቅር ምርጫየ የሙዝቃ ቪድዮ የተሰራው ነሀሴ 1996 ዓ.ም ነው። በዚህ ወቅት አብራው የነበረችው ሴት ደግሞ ዮዲት ናት።”

    ”ኤልያስ እንቅልፍ ውስዶታል። ፊትም ሙሉ በሙሉ ተቀያይሯል። በጤንነቱ ጊዜ የነበረው መልኩ ተመልሷል… ደነገጥኩ። በስመ አብ ወ ወልድ ብየ አማተብኩ። ኤልያስ! ኤልያስ… እያልኩ ተጣራሁ። ብንን ብሎ ፊቱን እየጠራረገ ቆንጆ ሕልም እያየሁ ነበር አቋረጥሽን አለኝ። ምን? አየህ ብየ ጠየኩት።

    በአራንጓዴ ሜዳ ላይ አንዲት ቀጭን መንገድ አገኘሁ በእሷ የሆነ በጣም የሚያምር ቦታ ደርሼ መጣሁ…”

    Add to cart
  • የወታደር ልጅ ነኝ

    $14

    Author: Shaleka Weynhareg Bekele

    Add to cart